በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና ለአፍሪካ የምትስጠው ብድር ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ከነበረው ዝቅተኛ ደርጃ ላይ ነው


ፎቶ ፋይል፦ የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ የብሪክስ ጉባኤ ላይ ደቡብ አፍሪካ (ፎቶ AP ነሐሴ 23፣ 2023)
ፎቶ ፋይል፦ የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ የብሪክስ ጉባኤ ላይ ደቡብ አፍሪካ (ፎቶ AP ነሐሴ 23፣ 2023)

ቻይና ለአፍሪካ የምትሰጠው ሉዓላዊ ብድር ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ከነበረው ዝቅተኛው ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ከቦስተን ዩኒቨርስቲ ዓለም አቀፍ የቻይና ተነሳሽነት ማዕከል የተገኘው መረጃ አመለከተ፡፡

መረጃው፣ ቤጂንግ ለአስርት ዓመታት በአህጉሪቱ ትኩረቷን አድርጋበት ከነበረው ትልቁ የመሠረተ ልማት ግንባታ ፊቷን ያዞረች መሆኑን ያሳያል ብሏል፡፡

የብድሩ ዝቅተኝነት የታየው በርካታ የአፍሪካ አገሮች ከከፍተኛ ዕዳ ቀውስ ለመውጣት እየታገሉ በሆኑበት ጊዜ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

የራሷ የቻይና ኢኮኖሚም ከፍተኛ ችግር እየገጠመው መሆኑ ተነግሯል፡፡ አፍሪካ የፕሬዚዳንት ሺጂፒንግ የ’ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ’ ትልቅ ትኩረት ሆና ቆይታለች፡፡

ቻይና ለአፍሪካ የምትሰጠውን ብድር የሚያሰላው የቦስተን ዩኒቨርሲቲ፣ የቻይና አበዳሪዎች ከ እ.አ.አከ2000 እስከ 2022 ለአፍሪካ 170 ቢሊዮን ዶላር መስጠታቸውን ገምቷል፡፡

ይሁን እንጂ የብድር መጠኑ እ.አ.አ ከ2016 ጀምሮ እየቀነሰ መምጣቱን አመልክቷል፡፡ ባላፈው ዓመት ለዘጠኝ ብድሮች የተሰጠው ጠቅላላ ገንዘብ 994 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን፣ ይህ ቻይና ብድር መስጠት ከጀመረችበት እ.አ.አ 2004 ወዲህ ዝቅተኛው ነው ተብሏል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG