በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና በአዲሱ ቀረጥ ጉዳይ ዩናይትድ ስቴትስን አሰጠነቀቀች

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ትረምፕ አስተዳደር ገቢ ንግድ አስመልክቶ የሚሰነዘረውን ዛቻ ተግባራዊ ካደረገ እኔም ከዩናይትድ ስቴትስ በሚመጣ ሥድሳ ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገቢ ንግድ ላይ አዲስ ቀረጥ እስከፍላለሁ ስትል ቻይና አስጠነቀቀች።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ትረምፕ አስተዳደር ገቢ ንግድ አስመልክቶ የሚሰነዘረውን ዛቻ ተግባራዊ ካደረገ እኔም ከዩናይትድ ስቴትስ በሚመጣ ሥድሳ ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገቢ ንግድ ላይ አዲስ ቀረጥ እስከፍላለሁ ስትል ቻይና አስጠነቀቀች።

ቻይና ማስጠንቀቂያውን የሰጠችው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዎ ዛሬ ዓርብ ሲንጋፖር ውስጥ የቻይናን የመንግሥት አማካሪ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪን ካነጋገሩ ከጥቂት ጊዜ በኋላ መሆኑ ታውቋል።

ሁለቱ ባለሥልጣናት ውይይታቸውን ካበቁ በኋላ ጋዜጠኞችን አላነጋገሩም። ውይይታቸውን ከመጀመራቸው በፊትም ጋዜጠኞቹ እንዲወጡ ተደርጎ እንደነበር ተገልጿል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG