በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና በአስከፊ የመሬት መንቀጥቀጥ ለተፈናቀሉ ጊዜያዊ ቤቶችን ማቋቋም ጀመረች


ቻይና በአስከፊ የመሬት መንቀጥቀጥ ለተፈናቀሉ ጊዜያዊ መጠለያ
ቻይና በአስከፊ የመሬት መንቀጥቀጥ ለተፈናቀሉ ጊዜያዊ መጠለያ

· የመሬት መንቀጥቀጡ 14ሺሕ ቤቶችን ሲያወድም ቢያንስ 144 ሰዎች ሞተዋል

በቻይና 14 ሺሕ መኖሪያ ቤቶችን ባወደመውና ቢያንስ የ144 ሰዎችን ሕይወት ባጠፋው አስከፊ የመሬት መንቀጥቀጥ የተፈናቀሉ ሰዎች እንዲጠለሉባቸው፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ባለአንድ ክፍል ቤቶች፣ በሰሜን ምዕራብ ቻይና በግንባታ ላይ እንደኾኑ፣ የአገሪቱ መንግሥት ብዙኀን መገናኛ አስታውቋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ፣ በሬክተር ስኬል ሲለካ 6ነጥብ2 እንደኾነ ሲመዘገብ፣ ከቻይና ዋና ከተማ ቤጂንግ በስተደቡብ ምዕራብ፣ 1ሺሕ300 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙ ተራራማ ስፍራዎች ላይ ነው ጉዳት ያደረሰው።

የመሬት መንቀጥቀጡ ያስከተለው ከባድ የጭቃ መንሸራተት ከቀበራቸው ሁለት መንደሮች ውስጥ፣ ሰውን በሕይወት ለማትረፍ የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች፣ ቁፋሮዋቸውን እንደቀጠሉ ናቸው፡፡ እስከ አኹን የሟቾች ቁጥር በዘጠኝ ከፍ እንዳለና ሦስት ሰዎች የደረሱበት እንደማይታወቅ፣ የቺንጋሃአይ ከተማ ባለሥልጣን፣ ዐርብ ዕለት አስታውቀዋል።

መንግሥታዊው ሲሲቲቪ፣ ከባድ የዕቃ ማንሻ መኪኖች፣ ቀደም ብለው በፋብሪካ የተሠሩ ነጭ እና ሣጥን መሰል መኖሪያ ቤቶችን እያነሡ ገላጣ ሜዳ ላይ በመደዳ ሲያስቀምጧቸው አሳይቷል፡፡ በዚኽም፣ እስከ አኹን 260 ቤቶች ለመቆም ችለዋል። እስከ ዐርብ ድረስ፣ በተዘጋጁ ዘጠኝ ቦታዎች ላይ የሚደረደሩት ቤቶችም፣ 500 ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሰኞ ምሽት በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ የተፈናቀሉት ከ87 ሺሕ በላይ ሰዎች፣ ላልተወሰነ ጊዜ ቤት አልባ ኾነው ይቆያሉ፡፡ አብዛኞቹ፣ እጅግ በጣም በሚቀዘቅዘው የአየር ኹኔታ፣ በሰማያዊ ፕላስቲክ መጠለያዎች ውስጥ ለመቆየት ተገደው ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG