በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና ወደ ሰሜን ኮርያ ልዩ ልዑክ ልትልክ ነው

Business leaders shake hands during signing ceremony attended by U.S. President Donald Trump and China's President Xi Jinping at the Great Hall of the People in Beijing, Nov. 9, 2017.
Business leaders shake hands during signing ceremony attended by U.S. President Donald Trump and China's President Xi Jinping at the Great Hall of the People in Beijing, Nov. 9, 2017.

ቻይና በያዝነው ሳምንት ወደ ሰሜን ኮርያ ልዩ ልዑክ እንደምትልክ ታውቋል።

ቻይና በያዝነው ሳምንት ወደ ሰሜን ኮርያ ልዩ ልዑክ እንደምትልክ ታውቋል።

ቻይና በቅርቡ ስላከናወነችው ብሔራዊ ኮንግረስ ከሰሜን ኮርያ ጋር ለመወያየት ስትል የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ሶንግ ታኦን በመጪው አርብ ወደ ሰሜን ኮርያ እንደሚሄዱ ኦፊሴላዊው ሽንዋ የዜና አገለግሎት ዘግቧል። ዘገባው ስለጉብኝቱ በዝርዝር የገለፀው ነገር የለም።

ቻይና ዋናዋ የሰሜን ኮርያ የንግድ አጋር ነች። ቅርብ የዲፕሎማስያዊ ግንኙነትም አላቸው። ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ግን የሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ውጥረት ተንፀባርቆበታል።

ቻይና ሰሜን ኮርያ በምታሳየው የእምቢተኛንነት ባህሪ ደስተኛ አይደለችም። ሰሜን ኮርያ የተጣሉበትን በርካታ ዓለምቀፍ ማዕቀቦችን ችላ በማለት የኑክሌርና የቦሊስቲክ ሚሳይል ሙከራዎች ማድረግዋ ቻይናን አሳዝኗል። ስለሆነም ቻይና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሰሜን ኮርያ ላይ የጣላቸውን በርካታ ማዕቀቦችን ደግፋለች።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG