ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትሱ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ እና የቻይናው ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ዛሬ ቤይጂንግ ውስጥ ባካሄዱት ስብሰባ፣ የሁለም ሀገሮች የወደፊት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት፣ አንዱ የሌላውን ወገን በማይጎዳ መልኩ እንዲሆን ጥሪ አቀረቡ።
ዩናይትድ ስቴትስ ከታይዋን ጋር በምታደርገው ግንኙነት፣ በንግዱ ዘርፍ ያለውን ውጥረት የሚያባብስ በመሆኑ ሁኔታው ቻይናን እንደማያስደስታት ዋንግ ዪ አመልክተው፣ ይህም በሁለቱ ሀገሮች መካከል ትምምን እንዳይኖር ስላደረገ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ከዚህ አድራጎቷ እንድትቆጠብ አሳስበዋል።
ፖምፒዮ በበኩላቸው፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ስለ ቻይና የተወሰኑ ስጋቶች እንዳሏት አመልክተው፣ እነዙህንም ወደ ውይይቱ ጠረጴዛ ለማምልጣት ፈቃደኛ እንደሆኑ ገልጸዋል።
ፖምፒዮ ወደ ቻይና ያመሩት፣ በደቡብ ኮሪያ ጉዟቸው፣ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር ከተገናኙ በኋላ መሆኑም ታውቋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ