በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ለሚደርስባቸው ሀገሮች መዋጮ “አልከፍልም” አለች


ፎቶ ፋይል - በማዕከላዊ ቻይና ሻንዚ ግዛት ውስጥ በሄጂን የሚገኝ የድንጋይ ከሰል ማቀነባበሪያ እአአ 11/28/2019
ፎቶ ፋይል - በማዕከላዊ ቻይና ሻንዚ ግዛት ውስጥ በሄጂን የሚገኝ የድንጋይ ከሰል ማቀነባበሪያ እአአ 11/28/2019

ቻይና በአየር ንብረት ለውጥ የተነሳ ጉዳት እና ውድመት ለሚደርስባቸው ታዳጊ ሀገሮች የሚውል የገንዘብ መዋጮ “አልከፍልም” አለች፡፡

ቻይና ትናንት ይህን ያለችው ግብጽ ሻርም ኤል ሼኽ ላይ እየተካሄደ በሚገኘው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ላይ ግዙፍ የካርቦን ወደከባቢ አየር የምትለቅቅ በመሆኗ ሓላፊነት አለባት ሲሉ ትናንሾቹ ደሴት ሀገሮች ካሳሰቡ በኋላ ነው፡፡

የአንቲጓ እና ባርቡዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋስተን ብራውን የትናንሽ ደሴት ሀገሮችን ማኅበር ወክለው ባደረጉት ንግግር ቻይና እና ህንድ ዋናዎቹ በካይ ጋዝ አመንጪ ሀገሮች እንደመሆናቸው ለጉዳት ለሚጋለጡ ደሆች ሀገሮች ካሳ የሚሆን ገንዘብ ማዋጣት አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የቻይናው የአየር ንብረት ጉባዔው ልዑክ ሺ ዢንሁዋ መዋጮ መሰብሰቡን እንደግፋለን እኛ ግን ገንዘብ አናዋጣም ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG