በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይና ኢኮኖሚ ዕድገት በእጅጉ ማሽቆልቆሉ ተገለጸ


ፎቶ ፋይል፦ ቤጂንግ ውስጥ የሚገኝ የገበያ አዳራሽ
ፎቶ ፋይል፦ ቤጂንግ ውስጥ የሚገኝ የገበያ አዳራሽ

የቻይና ኢኮኖሚ ዕድገት ከአርባ ዓመታት በሚበልጥ ጊዜ ታይቶ በማያውቅ መጠን መቀነሱ ተገልጿል። የዚህ ምክንያቱ የኮቪድ19 ዓለም አቀፍ ወረርሺኝን ለመዋጋት የተከተለችው ጥብቅ ፖሊሲ መሆኑ ተመልክቷል።

የቻይና ብሄራዊ የስታቲስቲክስ ቢሮ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት እንዳስታወቀው እአአ ባለፈው 2022 ኢኮኖሚው ያደገው በ3 ከመቶ ብቻ መሆኑን ጠቁሟል። በቀደመው እአአ 2021 በ8 ነጥብ 1 ከመቶ አድጎ እንደነበር መረጃው ይጠቁማል።

እአአ በ1970ዎቹ ወዲህ ይህ ሁለተኛው ዝቅተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት መሆኑ ተጠቁሟል።

ቤጂንግ የኮቪድ19 ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስታ "ዜሮ ኮቪድ" በሚል ስያሜ የሚታወቅ ጥብቅ ኮሮና ቫይረስን የመከላከል እና መቆጣጠር ፖሊሲ ስራ ላይ እንዳዋለች ይታወሳል። በበርካታ የሀገሪቱ ከተሞች ፖሊሲውን በመቃወም ያልተለመደ ህዝባዊ ተቃውሞ መካሄዱን ተከትሎ መንግሥቱ በታህሳስ መጀመሪያ በድንገት ጥብቅ ጸረ ኮቪድ ፖሊሲውን ሰርዞታል።

የሆነ ሆኖ ባሁኑ ወቅት ወረርሽኙ በስፋት ያገረሸ ሲሆን እስካሁን ከ60 ሺህ የሚበልጡ ሰዎች እንደሞቱ ተዘግቧል።

XS
SM
MD
LG