በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከግብፅ እና ከአረብ ሊግ ባለሥልጣናት ጋር ተነጋገሩ


የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ፣ ከግብፁ አቻቸው ሳሜህ ሹክሪ ጋር
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ፣ ከግብፁ አቻቸው ሳሜህ ሹክሪ ጋር

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቺን ጋንግ ትናንት ዕሁድ በካይሮ ከግብፅ እና ከአረብ ሊግ ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተዋል።

ቺን ከግብፁ አቻቸው ሳሜህ ሹክሪ ጋር የተወያዩ ሲሆን ፕሬዚዳንቱ አብደልፋታህ ኤል ሲሲ እንዲሁም ከአረብ ሊግ ዋና ፀኃፊ አህመድ አቡል ጌይት ጋር ተነጋግረዋል።

የግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የቻይናው አቻቸው ባደረጉት የጋራ ጋዜጣዊ ጉባዔ የእስራኤል እና ፍልስጥዔምን ግጭት ጨምሮ በተለያዩ ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ገልፀዋል።

የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከግብጽ ፕሬዚዳንት ሲሲ ጋር ባደረጉት ውይይት ሀገራቸው በግብጽ የመሰረተ ልማት ፕሮጄክቶች መዋዕለ ነዋይ መመደቧን እንደምትቀጥል አውስተዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሀገራቸው በተፈጥሮ ሀብት በከበረችው በአፍሪካ አህጉር ያላትን ተሳትፎ ለማጠናከር በታለመው ጉብኝታቸው ኢትዮጵያን፣ ጋቦንን፣ አንጎላን እና በኒንን ከጎበኙ በኋላ ጉብኝታቸውን በግብፅ አጠናቅቀዋል።

ቺን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነቱን ከያዙ ወዲህ የመጀመሪያ የውጭ ጉብኝታቸው ሲሆን በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከአፍሪካ ህብረት ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተዋል።

XS
SM
MD
LG