በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ ለመደራደር ዝግጁ ነች” - ፑቲን


የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን
የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን

በዩክሬን በመካሄድ ላይ ያለውን ጦርነት በተመለክተ ሩሲያ ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ቻይናን ለመጎብኘት ዝግጅት ላይ ባሉበት ዋዜማ አስታውቀዋል።

ለመንግሥታዊው ሺንዋ ዜና አገልግሎት ቃለ መጠይቅ የሰጡት ፑቲን፣ “ሩሲያ ድርድርን ተቃውማ አታውቅም፣ ለግጭቱ በሰላማዊ መንገድ፤ ሁሉን አቀፍ፣ ዘላቂና ፍትሃዊ መፍትሄ እንዲገኝ ሩሲያ ትሻለች” ማለታቸው ተጠቅሷል።

ፑቲን፤ ሩሲያ በዩክሬን የምታካሂደውን ጦርነት በምትደግፈው ቻይና የሚያደርጉት ጉብኝት የመጣው፣ የሃገራቸው ጦር በዩክሬን ሰሜን ምሥራቅ ካርኪቭ ክልል ጥቃቱን ባጠናከረበት ወቅት ነው።

ቻይና በጉዳዩ ላይ ገለልተኛ አቋም እንዳላት ብታስታውቅም፣ “ሩሲያ ዩክሬንን ያጠቃቸው በምዕራቡ ዓለም ትንኮሳ ምክንያት ነው” የሚለውን የሞስኮ መከራከሪያ ትቀበላለች።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG