በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና እና ሩሲያ በጋራ የጦር ልምምድ ትብብራቸው እያጠናከሩ እንዳሉ ተንታኞች ጠቆሙ


ቻይና እና ሩሲያ፣ በጃፓን ባሕር ላይ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ እያደረጉ እንደኾነ ተነገረ፡፡
ቻይና እና ሩሲያ፣ በጃፓን ባሕር ላይ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ እያደረጉ እንደኾነ ተነገረ፡፡

የዩክሬን ጦርነት እየተፋፋመ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ ቻይና እና ሩሲያ፣ በጃፓን ባሕር ላይ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ እያደረጉ እንደኾነ ተነገረ፡፡

ተንታኞች፣ የጦር ልምምዱ፥ ሁለቱ አገሮች ወታደራዊ ትብብራቸውን እያጠናከሩ መኾናቸውን እንደሚያሳይ አመልክተዋል፡፡

አያይዘውም፣ የጦር ልምምዱ፥ በአካባቢው እያደገ የመጣውን የዩናይትድ ስቴትስንና የአጋሮቿን ትብብር ለመገዳደር የሚያደርጉት ጥረት አካል ነው፤ ሲሉ፣ ተንታኞቹ አክለዋል፡፡

በዓለም አቀፍ የክርስቲያን ዩኒቨርሲቲ የአካባቢ ደኅንነት ባለሞያ ስቴፈን ናጊ፣ “ሩሲያ እና ቻይና፣ ጃፓንና ዩናይትድ ስቴትስ፣ በኔቶ እና በሕንድ ፓስፊክ ክልል በሚያሳዩት ትብብር ደስተኛ እንዳልኾኑ ለማሳየት እየሞከሩ ነው፤” ሲሉ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ናጊ በተጨማሪም፣ “እነርሱም በአካባቢው፣ እንደ ዋሽንግተንና አጋሮቿ ተመሳሳይ የጦር ትብብር ማሳየት እንደሚችሉ ማረጋገጥ ይፈልጋሉ፤” ብለዋል፡፡

ሩሲያውያንም፥ አሁንም በምሥራቅ ግንባር ያሉትን ግጭቶች የመቆጣጠር ዐቅም እንዳላቸውና በኢንዶ-ፓሲፊክ ክልል ከቻይና ጋራ በመሥራት፣ በዩናይትድ ስቴትስ ላይ ጫና ለመፍጠር የሚያስችል ዐቅም እንዳላቸው፣ በተለይም በጃፓን ደጃፍ፣ ትልቅ ችግር መፍጠር እንደሚችሉ ለማሳየትም ጭምር ልምምዱን እንደሚያደርጉ፣ ናጊ ገልጸዋል፡፡

የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ፣ ዛሬ ኀሙስ በአወጣው መግለጫ፣ የልምምዱ ዋና ዓላማ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን “የባሕር ኃይል ትብብርን ማጠናከር" እና "በእስያ ፓስፊክ ውቅያኖስ ሰላምንና መረጋጋትን ማስጠበቅ” ነው፤ ብሏል።

ሩሲያ እና ቻይና በልምምዱ፣ ከ10 በላይ የባሕር ኃይል መርከቦችንና ከ30 በላይ የጦር አውሮፕላኖችን ማሠማራታቸው ተገልጿል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG