ቻይና በቤልት ኤንድ ሮድ በተባለው የመሠረት ልማት ግንባታ (BRI) ማዕቀፍ ውስጥ በቻይና-አፍሪካ የትብብር ውጤቶችን የያዘ ሪፖርት አሳተመች።
ሪፖርቱ 52 የአፍሪካ ሀገራት እና የአፍሪካ ህብረት ከቻይና ጋር በቤልት ኤንድ ሮድ ትብብር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል ብሏል።
“ቻይና እና አፍሪካ የመሠረተ ልማት ትስስራቸውን ወደ አዲስ ደረጃ ከፍ አድርገዋል” ይላል ዘገባው::
የቻይና ኩባንያዎች ከ10,000 ኪሎ ሜትር በላይ የባቡር መስመር ዝርጋታ፣ ወደ 100,000 ኪሎ ሜትር የሚጠጉ አውራ ጎዳናዎች፣ በግምት 1,000 ድልድዮች፣ 100 ወደቦች፣ 66,000 ኪሎ ሜትር የሃይል ማመንጫዎችን በመገንባት እና በመለወጥ ላይ መሆናቸውን ሪፖርቱ ጠቁሟል። በመላው አፍሪካ 150,000 ኪሎ ሜትር የመገናኛ አውታሮች መዘርጋቱም ተጠቅሷል፡፡
መድረክ / ፎረም