በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና ውስጥ በመሬት ርዕደት ቢያንስ 127 ሰዎች ሞቱ


ቻይና ሰሜን ምዕራባዊ ክፍለ ግዛት ውስጥ በደረሰ የመሬት ርዕደት ቢያንስ 127 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ፡፡
ቻይና ሰሜን ምዕራባዊ ክፍለ ግዛት ውስጥ በደረሰ የመሬት ርዕደት ቢያንስ 127 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ፡፡

ቻይና ሰሜን ምዕራባዊ ክፍለ ግዛት ውስጥ በደረሰ የመሬት ርዕደት ቢያንስ 127 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ፡፡ ርዕደቱ በሪክተር ስኬል መለኪያው ላይ 6 ነጥብ 2 ያስመዘገበ እንደነበር የሀገሪቱ የዜና ማሰራጫዎች ዘግበዋል፡፡

ትናንት ሰኞ ዕኩለ ሌሊይ ላይ በደረሰው የመሬት መናወጥ ጋንዙ ክፍለ ግዛት ውስጥ 113 ኪንኻይ ክፍለ ግዛት ውስጥ ደግሞ 14 ሰዎች መሞታቸውን ቻይና ዴይሊ ዘግቧል፡፡ 700 ሰዎች ቆስለዋል፡፡

የአጣዳፊ እርዳታ ሠራተኞች በአደጋው የደረሱበት የጠፉ ሰዎችን በፈራረሱ ህንጻዎች ውስጥ እየፈለጉ ናቸው፡፡ በነውጹ ሳቢያ ቢያንስ በአንድ አካባቢ የመሬት መናድ አደጋ የደረሰ ሲሆን በዚያም ውስጥ የተቀበሩ ሰዎች ይኖሩ እንደሆን በሚል ፍለጋ ቀጥሏል፡፡

በመሬት ርዕደቱ መኖሪያ ቤቶቻቸው የፈረሱባቸው ነዋሪዎች የክረምቱን ቅዝቃዜ በጥድፊያ በተተከሉ ድንኳኖች ማሳለፍ ግድ ሆኖባቸዋል፡፡

የጋንዙ ክፍለ ግዛት የአጣዳፊ እርዳታ ሠራተኞች 300 ተጨማሪ ሠራተኞች እንዲላኩላቸው የጠየቁ ሲሆን የኪንኻይ ባልስልጣናት በበኩላቸው የመሬት መናድ በደረሰበት አካባቢ 20 ሰዎች የደረሱበት እንዳልታወቀ አመልክተዋል፡፡

የዛሬው የመሬት መናወጥ በሀገሪቱ በዘጠኝ ዓመታት ውስጥ ከደረሱት ሁሉ ከባዱ መሆኑ ታውቋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG