በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና በኒቪዲያ ኩባንያ ላይ የጸረ ገበያ ጠቅላይነት ምርመራ ጀመረች


ኒቪዲያ ኩባንያ
ኒቪዲያ ኩባንያ

ቻይና፣ በዩናይትድ ስቴትስ የቺፕ አምራች የሆነው ኒቪዲያ ኩባንያ ገበያውን ሙሉ ለሙሉ በመቆጣጠር የሀገሪቱን የፀረ-ገበያ ጠቅላይ ሕግ ተላልፏል ስትል ምርመራ መጀመሯን ዛሬ ሰኞ አስታውቃለች። ውሳኔው ዋሽንግተን በቅርቡ በከፊል ኤሌክትሪክ አስተላላፊ የሆኑ ቺፕ አምራቾች ላይ ለጣለችው እገዳ የበቀል እርምጃ ተደርጎ እንደሚታይ ተገልጿል።

የቻይናን ገበያ የሚቆጣጠረው ተቋም ባወጣው መግለጫ፣ ኒቪዲያ የተሰኘው ኩባንያ ሜላኖክስ የተሰኘውን የቴክኖሎጂ ተቋም በገዛበት ወቅት ስምምነት የተደረሰባቸውን ኃላፊነቶች መጣሱን አስታውቋል። የቻይና የጸረ ገበያ ጠቅላይነት ሕግ በምን መልኩ እንደጣሰ ግን አላብራራም።

ሶፍትዌሮችን እና ሃርድዌሮችን በሰው ሰራሽ ልህቀት በማምረት የሚታወቀው ኒቪዲያ በጉዳይ ላይ ምላሽ ባይሰጥም፣ የቻይናን ውሳኔ ተከትሉ የኩባንያው አክሲዮን ግብይት በ2.2 ከመቶ መቀነሱ ተመልክቷል።

ቻይና ምርመራ ማካሄድ የጀመረችው፣ ዩናይትድ ስቴትስ ባለፈው ሳምንት በቻይና ከፊል የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ኢንዱስትሪ ላይ ዘመቻ ከጀመረች በኃላ ነው። የኒቪዲያ የቺፕ ምርቶች በቻይና ከፍተኛ ፍላጎት የነበራቸው ቢሆንም ዩናይትድ ስቴትስ፣ ቻይና ዘመናዊ እና የተሻሻሉ ቺፖችን እንዳታገኝ የምታደርገው ጥረት ኩባንያውን ክፉኛ ጎድቶታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG