ኬንያ ከቻይና ጋራ ያላትን የንግድ እና የብድር ግንኙነት አስመልክቶ፣ የኬንያውያን ክርክር ተጋግሎ ቀጥሏል፡፡
በናይሮቢ የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ፣ በሰፊው እየደገሰ በመጋበዝ፣ ኬንያውያን ከቻይናውያን ጋራ ያላቸውን ባህላዊ ትስስር ለማጎልበት ጥረት በማድረግ ላይ ነው፡፡
የሁለቱ አገሮች ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ሚዛን ያጋደለ እንደኾነ የሚናገሩት ተንታኞች ደግሞ፣ የኤምባሲው ጥረት፣ ኬንያውያን የሚያሰሙትን ቅሬታ ለማርገብ የታለመ ነው፤ ይላሉ፡፡
ቪክቶሪያ አሙንጋ ከናይሮቢ ተጨማሪ አላት፡፡ ቆንጅት ታየ ወደ ዐማርኛ መልሳዋለች፡፡
መድረክ / ፎረም