በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና በእስያ የአሜሪካን F-35s ለመቋቋም የራሷን J-20 ጄቶች አሰማራች


ጄ 20 የተሰኘው የቻይና የጦር አውሮፕላን
ጄ 20 የተሰኘው የቻይና የጦር አውሮፕላን

ቻይና በእስያ እየጨመረ የመጣውን የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ተሳትፎ ለመቋቋም ዋነኞቹን ተዋጊ ጀቶችዋን በባህር ዳርቻዎች ማሰማራቷ ተነገረ፡፡

እዚያው ቻይና ስሪት የሆነውና ቼኝዱ ጄ 20 የተሰኘው የጦር አውሮፕላን በአገሪቱ በስተደቡብ በሚገኙት የደቡብ ቻይናና እና ምስራቅ ቻይና ባህሮች እንዲሁም በታይዋን ዙሪያ መሰማራታቸውን ባለሙያዎች ከእስያ መግለጻቸው ተመልክቷል፡፡

የቻይና መንግሥት በሚቆጣጠረው የግሎባል ታይምስ ድረገጽ ላይ እኤአ ሚያዝያ 13 የወጣ ዘገባ የጄ 20 ጀቶች “ሁለቱን ባህሮች ለመቆጣጠር የተለመደውን የዘወትር ልምምድ ለማድረግ ተሰማርተዋል” ሲል የቤጂንግ መንግሥት ማስታውቁ ተዘግቧል፡፡ መሰረቱን ዋሽንግተን ያደረገውና እስያ ማሪታይም ትራንፓረንሲ የተባለው ተቋም ዳይሬክተር ግሪጎሪ ፖሊንግ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በታይዋን ወይም በምስራቅ ቻይና ባህር ከምታደርገው እንቅስቃሴ ጋር ይህ መሳ ለመሳ የሚሄድ ነው ብለዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አልፎ አልፎ በእስያ የውዝግብ ቀጠና በሆኑት የባህር ክልሎች የሚያስተላልፋቸው የጦር መርከቦች ያሉ ሲሆን፣ባላፈው ጥር ወር የጦር ጄት አውሮፕላን ተሸካሚ የሆኑ ሁለት መርከቦችን ወደ ደቡብ ቻይና ባህር መላኳ ተገልጿል፡፡

ዩናዩትድ ስቴትስ የእስያ ፓስፊክ አጋር አገሮች አውስትራሊያ፣ ጃፓንና ደቡብ ኮሪያ የተባለውን F-35s የጦር ጀቶችን የገዙ ሲሆን ሲንጋፑርና ታይላንድም በቅርቡ እንደሚከተሉ ተነግሯል፡፡

XS
SM
MD
LG