በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና በግድያ በተከሰሰ አንድ አሜሪካዊ ላይ የሞት ፍርድ አስተላለፈች


አንድ የፖሊስ መኮንን የኤንፒሲ ስብሰባ አዳራሽ አቅራቢያ ዘብ ቆሞ መጋቢት 5/2021
አንድ የፖሊስ መኮንን የኤንፒሲ ስብሰባ አዳራሽ አቅራቢያ ዘብ ቆሞ መጋቢት 5/2021

የቻይና ፍርድ ቤት የሴት ጓደኛውን በስለት በመውጋት ገድሏል በተባለ አንድ አሜሪካዊ ላይ የሞት ፍርድ መበየኑ ተገለጸ፡፡ ፍርድ ቤቱ ሻዲድ አብዱልማቲን የተባለው ግለሰብ ባላፈው ዓመት ቼን የተባለችውን የ21 ዓመት ሴት ልጅ ፊቷንና አንገቷን በስለት ደጋግሞ በመውጋት በመግደሉ ጥፋተኛ ሆኖ መገኘቱን አስታውቋል፡፡

ሻዲድ ግድያውን የፈጸመው በሁለቱ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ቂም ይዞ በመቆየቱ መሆኑን ተገልጿል፡፡ በቻይና የሚገኘውን የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አስተያየት ለማገኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

አንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣን ግን መንግሥታቸው ጉዳዩን እየተከታተለው መሆኑን ጠቅሰው የግለሰቦችን ምስጢር ለመጠበቅ ተጨማሪ አስተያየት እንደማይስጡ ማስታወቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ ቻይና በየዓመቱ በብዙ እስረኞች ላይ የሞት ፍርድ ማስተላለፏ ከሌላው ዓለም በተለይ ሁኔታ የተለመደ ቢሆንም፣ በምዕራባውያን ላይ የሚተላለፈው የሞት ውሳኔ ግን ብዙም የተለመደ አለመሆኑን አስታውቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG