በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይና እና የአውሮፓ ኅብረት መሪዎች በንግድ እና ዩክሬን ጉዳይ ውይይት ተቀምጠዋል


የቻይና ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ
የቻይና ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ

የቻይና እና የአውሮፓ ኅብረት ምሪዎች አጨቃጫቂ በሆነው የንግድ ግኑኘታቸው ላይ እንዲሁም ዩክሬንን በተመለከተ ለመወያየት፣ ዛሬ ሐሙስ ስብሰባ መቀመጣቸው ታውቋል።

የቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ ከአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኡርሰላ ቮንደር ላይን እንዲሁም ከኅብረቱ ም/ቤት ፕሬዝደንት ቻርለስ ሚሼል ጋር እንደተገናኙ የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

ከ200 ቢሊዮን ዶላር በላይ ይደርሳል የተባለውን የንግድ አለመመጣጠን ለማስተካከል፣ ቻይና ገበያዋን እንድትከፍት የአውሮፓ ኅብረት ይሻል። ሁለቱ የኅብረቱ መሪዎች ይህንኑ ለሺ ጂንፒንግ በግልጽ እንደነገሯቸው ተዘግቧል።

ቻይና በበኩሏ ኅብረቱ ለውጪ ገበያ በሚቀርቡ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ ያስቀመጠው ማነቆ እንዲሁም፣ ለኤሌክትሪክ መኪናዎች የሚሰጠውን ድጎማ በተመለከተ ኅብረቱ ምርመራ መጀመሩ እንዳላስደሰታት ታውቋል።

ስብሰባው የመጣው፣ ጣልያን በቻይና እየተመራ ካለውና ዓለምን በመንገድ፣ በወደቦች እና በኃይል ማመንጫዎች ለማስተሳሰር ካቀደው የ”ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ” ከተሰኘው ፕሮጀክት ለቃ መውጣቷን ባስታወቀች ማግስት ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG