በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይና-አፍሪካ ትብብር ጉባኤ ተጀመረ


የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው
የቻይና-አፍሪካ ትብብር ጉባኤ ተጀመረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:10 0:00

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ50 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች የታደሙበት የቻይና-አፍሪካ የትብብር ጉባዔ ዛሬ በቤጂንግ ተከፍቷል። ለሦስት ቀናት በሚካሔደው በዚህ ጉባኤ ላይ፣ እስከ አውሮፓውያኑ 2027 በሚኖረው የቻይና እና አፍሪካ ግንኙነት የትብብር ሰነዶች ላይ ውይይት ተደርጎ ስምምነት እንደሚፈረም ይጠበቃል፡፡

በጉባኤው ለመሳተፍ ቤጂንግ ከገቡ የአፍሪካ መሪዎች አንዱ የሆኑት፣ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ቻይና አበርክታለች ያሉትን ድጋፍ አድንቀዋል፡፡

ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ የታየው ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ጤናማ እንዳልሆነ የሚገልፁት የፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ተንታኝ አቶ ሸዋፈራው ሽታሁን ለዚህም ምክንያናቱን አብራርተዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG