ትላንት እሑድ፣ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ቢጂንግ የገቡት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶር.)፣ ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ቺያንግ ጋራ፣ በምጣኔ ሀብት ገዳዮች ላይ እንደተወያዩ ጽ/ቤታቸው ገልጿል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት፣ ኢትዮጵያ እየተፈተነችበት ባለው የዕዳ ጫና ማቃለል ላይ ሊያተኩር እንደሚችል፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህር እና ተመራማሪው ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገዳ፣ ወቅታዊ ጉዳዮችን መነሻ በማድረግ አብራርተዋል፡፡
ከአይኤምኤፍ እና ከዓለም ባንክ ጋራ፣ ከዕዳ ጫና ጋራ በተያያዘ ለሚደረገው ድርድር ስኬታማነትም፣ የቻይና ሚና አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ፣ ከቻይና በኋላ ከሌሎች አበዳሪዎችም ከዕዳ ክፍያ የእፎይታ ጊዜ እንደምትፈልግ፣ የአይኤምኤፍ ባለሥልጣን፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ አስታውቀዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም