በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና የመከላከያ ሚኒስትሯ ከአሜሪካ አቻቸው እንዲገናኙ መጋበዟን አልተቀበለችም


ፎቶ ፋይል፦ የፔንታገን ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል ፓት ራይደር
ፎቶ ፋይል፦ የፔንታገን ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል ፓት ራይደር

የዩናይትድ ስቴትሱ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን ከቻይናው አቻቸው ሊ ሻንግፉ ጋራ በሲንጋፖር ተገናኝተው እንዲመክሩ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ያቀረበችውን የስብሰባ ግብዣ፣ ቻይና ውድቅ ማድረጓን ፔንታገን አስታወቀ፡፡

የፔንታገን ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል ፓት ራይደር፣ “ቻይና፣ በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ ኦስተን ከከቻይናው የመከላከያ ሚኒስትር ሊ ጋራ፣ በዚኽ ሳምንት፣ ሲንጋፖር ውስጥ እንዲገናኙ ያቀረብነውን ግብዣ ውድቅ ማድረጓን፣ ዛሬ ሌሊቱን፣ ለዩናይትድ ስቴትስ አስታውቃለች፤” ሲሉ፣ ከትላንት በስቲያ ሰኞ በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል፡፡

ቻይና ስብሰባውን አለመቀበሏ፣ “ዩናይትድ ስቴትስ፥ በሁለቱ የመከላከያ ኃይሎች መካከል ትርጉም ያለው ግንኙነት እንዲኖር ያላትን ፍላጎት አይለውጠውም፤ እንዲሁም ከቻይና ሕዝባዊ ነፃ አውጪ ሠራዊት ጋራ፣ ክፍት የግንኙነት መሥመር እንዲኖር የምታደርገውን ጥረት አይቀንሰውም፤” ሲሉ ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው አክለዋል፡፡

የቻይናው ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ፣ ትላንት ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ፣ በቻይና እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ወታደራዊ ግንኙነት ለማድረግ፣ “አሁን ያሉት አስቸጋሪ ኹኔታዎች ለምን እንደተፈጠሩ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በግልጽ ታውቀዋለች፤” ብለዋል፡፡

ሊ፣ እ.ኤ.አ. በ2018፣ የሩሲያን የጦር መሣሪያዎች ገዝተዋል፤ በሚል፣ በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ማዕቀብ ተጥሎባቸው እንደነበር ተገልጿል፡፡

ይኹን እንጂ፣ ይህ ማዕቀብ፣ ሎይድ ኦስተንን ከሊ ጋራ የኦፊሴል ሥራቸውን እንዳይሠሩ አያግዳቸውም፤ ተብሏል፡፡

ይህ ዐይነቱ ውሳኔ፣ እ.ኤ.አ ከ2021 ወዲህ፣ ቻይና የስብሰባ ግብዣዎችን ላለመቀበል ከአቀረበቻቸው ሰበቦች ውስጥ፣ የቅርብ ጊዜው እንደኾነ ተመልክቷል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን፣ በዚኽ ሳምንት፣ በሻንግሪ ላ ውይይት ላይ ለመካፈል ወደ ሲንጋፑር ይጓዛሉ፡፡

XS
SM
MD
LG