በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይና ኮምዩኒስት ፓርቲና ሙስና


ከቻይና በሃያ ዓመታት 120 ቢልዮን ዶላር በሸሹ ባለሥልጣናት መዘረፉ ተዘገበ፡፡

ገዥው የቻይና ኮምዩኒስት ፓርቲ በውስጡ ሙስና እየበረታ መምጣቱን አመነ፡፡ በሙስና ላይ የሚያካሂደውን ውጊያ እንደሚያጠናክርም አስታወቀ፡፡

ባለሥልጣናት ጠበቅ ያለ ፍተሻና ክትትል እንደሚደረግባቸው የፓርቲው የሥነ-ሥርዓት ጉዳዮች ምክትል ሊቀመንበር ዉ ዩሊያንግ ዛሬ ገልፀዋል፡፡

ይህ የፓርቲው መግለጫ ከመውጣቱ ቀደም ብሎ ዜጎች በሙስና ውስጥ ተዘፍቀዋል ስለሚሏቸው ባለሥልጣናት ጥቆማና አስተያየት የሚሰጡባቸው ነፃና ገለልተኛ የተባሉ የኢንተርኔት አገልግሎቶች ተከፍተዋል፡፡

ከቤጂንግ የደረሰን ዘገባ የዛሬ የዴሞክራሲ በተግባር ርዕስ ነው፤ ያድምጡት፡፡

XS
SM
MD
LG