በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቻይና የውልደት መጠን በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል


ፎቶ ፋይል፦ ቤጂንግ፤ ቻይና
ፎቶ ፋይል፦ ቤጂንግ፤ ቻይና

በቻይና አንድ ቤተሰብ አንድ ልጅ ብቻ እንዲወልድ የሚያዘው የረጅም ጊዜ ፖሊሲን የሚያላላ መመሪያ የወጣ ቢሆንም፣ የኮሙዩኒስት ፓርቲው እኤአ በ1949 ሥልጣን ከተረከበ ወዲህ በቻይና የውልደት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ መምጣቱ ተመለከተ፡፡

ከብሄራዊ የስታትስቲክስ ቢሮ ዛሬ የወጣው ዘገባ እንዳመለከተው፣ የቻይና ህዝብ ብዛት እኤአ በ2021 መጨረሻ 1.4 ቢሊዮን ላይ ቆሟል፡፡

በተባለው የ2021 ዓመት ውስጥ የተወለዱት 10.6 ሚሊዮን ህጻናት ሲሆኑ በ1ሺ ቻይናውያን የወለዱት 7.52 ብቻ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

በቀደመው የ2020 ዓመት የተወለዱት 12 ሚሊዮን ህጻናት የነበሩ ሲሆን ከአንድ ሺዎቹ ቻይናውያን መካከል የወለዱት 8.52 መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በዚህ ስሌት መስረት የቻይና ህዝብ እድገት ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ0.34 መቀነሱ ተመልክቷል፡፡

አዲሱ የቻይና ፖሊሲ አንድ ቤተሰብ ወይም ጥንዶች እስከ ሁለት ልጅ መውለድ የሚችሉ መሆኑን ቢፈቅዱም እየተወደደ የመጣው ኑሮ ብዙዎችን ተጨማሪ ልጅ ከመውለድ ያገዳቸው መሆኑ ተዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG