በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ሾመች


ፎቶ ፋይል፦ የቻይና የጦር ሰፈር በጅቡቲ
ፎቶ ፋይል፦ የቻይና የጦር ሰፈር በጅቡቲ

ቻይና ዢው ቢንግ የተባሉትን ከፍተኛ ዲፕሎት ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ሶማሊያን ውስጥ ያሉ ግጭቶችን ጨምሮ ላልተረጋጋው የአፍሪቃ ቀንድ ቀጠና ልዩ መልዕክተኛ አድርጋ ሾማለች።

ዢው ከዚህ ቀደም በፓፓዋ ኒው ጊኒ የቻይና አምባሳደር ሆነው ሰርተዋል። በአፍሪካ፣ አሜሪካ እና ኦሺኒያ አህጉራት ውስጥ በመስረት ልምድ እንዳላቸው የሀገሪቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።

የልዩ ልዑኩ ግብ፣ ቀጠናውን ለዘላቂ መረጋጋት፣ ልማት እና ብልጽግና ያበቃል የተባለለትን የቻይናን “ሰላማዊ የልማት ዕቅድ ማስተዋወቅ እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ዋንግ ዊንቢን በቤጂንግ በነበረ እለታዊ ማስገንዘቢያ ላይ ተናግረዋል።

ቻይና ዓለም አቀፉን ቁልፍ የመርከብ መስመር የምትከታተልበት የጂቡቲ የጦር ሰፈሯን ጨምሮ፣ ከአፍረካ ቀንድ ጋር የጥቅም ትስስር አላት። ንግድን በተመለከተ በጂቡቲ ወደብ ላይ ለተመረኮዘቸው ወደብ አልባ ሀገር ኢትዮጵያም ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ አበድራለች።

ቀጠናው በተጨማሪም፣ ቻይና በነዳጅ ማውጣት ሥራ በተሰማራችበት ደቡብ ሱዳን ውስጥ ባለው አለመረጋጋት እንዲሁም ከሶማሊያ እየተሻገረ በጎረቤት ሀገር ኬንያን የሰዎችን ነፍስ እየቀጠፈ ባለው ጥቃት ምክንያት አደጋ ተደቅኖበታል።

XS
SM
MD
LG