በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይና-አፍሪካ ኤክስፖ ስኬታማ እንደነበር ተገለጸ


ፎቶ ፋይል፦ የቻይናው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን
ፎቶ ፋይል፦ የቻይናው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን

ሦስተኛው የቻይና እና አፍሪካ የኢኮኖሚ እና የንግድ ኤክስፖ፣ ፍሬያማ ኾኖ እንደተጠናቀቀ፣ የቻይናው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አስታወቁ።

በቤጂንግ በተካሔደ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተናገሩት ቃል አቀባዩ ዋንግ ዌንቢን፣ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በተካሔደው የቻይና-አፍሪካ የኢኮኖሚ እና የንግድ ኤክስፖ፣ በሺሕዎች የሚቆጠሩ የቻይና እና የአፍሪካ ተሳታፊዎች ሁናን ላይ ተገናኝተው፣ ለቻይና እና አፍሪካ የወደፊት የጋራ እድገት ትልም አስቀምጠዋል፡፡

ኤክስፖው፥ የቻይና እና አፍሪካ ትብብርን በተመለከተ የተካሔደ ትልቁ ኤክስፖ እንደኾነ ተመልክቷል። ከአምስት ዓመታት በፊት የተጀመረው ዓመታዊ ኤክስፖ፣ ዘንድሮ፣ 1ሺሕ700 የቻይና እና የአፍሪካ ንግድ ተቋማትን፣ ማኅበራትንና የንግድ ም/ቤቶችን፣ የፋይናንስ ተቋማትን፣ ከ53 የአፍሪካ አገሮች፣ እንዲሁም ከ12 ዓለም አቀፍ ተቋማት እና 30 የቻይና ግዛቶችን አሳትፏል።

የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤቱ ቃል አቀባይ፣ “ቻይና ለአፍሪካ ወዳጆቿ ያላትን ታማኝነት ለዓለም የምታሳይበት ኤክስፖ ነው። ቻይና፣ ሥልጣኔዋን ለአፍሪካ ሀገራት ማጋራቷን ትቀጥላለች፤” ሲሉ ተደምጠዋል።

XS
SM
MD
LG