ቻይና በዓለምቀፉ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት፣ የኢኮኖሚ ቀበቶዋን እያጠበቀች ባለችበት በአሁኑ ወቅት፣ የአፍሪካ መሪዎች የመሰረተ-ልማቶች ውጥኖችና የንግድ መፃኢ ዕድል በአንዳንድ ሁኔታ ደግሞ የብድር እፎይታ ማግኘትን አስመልክቶ፣ የአፍሪካ መሪዎችን እያሳሰበ ነው ተብሏል።
ከቻይና የሚወጣውና ወደ ቻይና የሚገባው የንግድ መጠን፣ በዓመት ከ$200 ቢልዮን ዶላር በላይ እንደሚሆን ታውቋል። ቻይና ዋናዋ የአፍሪካ የንግድ አጋር እንደመሆኗ፣ ለአህጉሪቱ መንገዶችን፣ ወደቦችንና የባቡር ሃዲዶችን የመሳስሉትን መሰረተ-ልማቶችን ለመገንባት፣ በብዙ ቢልዮኖች ዶላር የሚገመት ብድር ሰጥታለች።
የቻይና ኢኮኖሚ በኮቪድ-19 ምክንያት ከባድ ጉዳት ደርሶበታል ይላሉ የን ሰን ስቲምሰን ማዕከል የተባለ ዋሺንግተን የሚገኝ፣ የፕሊሲ ጥናት ውስጥ፣ የቻይና ፕሮግራም ሥራ አስኪያጅ። በዚህ ምክንያትም ቻይና በፊት ታደርገው የነበረውን ያህል፣ ለአፍሪካም ሆነ የሌሎች ታዳጊ ሃገሮች መሰረተ-ልማቶችን ለመርዳትም ሆነ ገንዘብ ለማበደር የነበራትን አቅም ይቀንሳል ብለዋል።
የቻይና መንግሥት ባንኮችና የግል ባለሃብቶች፣ በ17 ዓመታት ውስጥ $146 ቢልዮን ዶላር የሚሆን ገንዘብ፣ ለአፍሪካ ሃገሮች አበድረዋል። በኮቪድ-19 ምክንያትም፣ በርካታ የአፍሪካ ሃገሮች፣ የዕዳ ክፍያው ጊዜ እንዲገፋላቸው ወይም እንዲሰረዝላቸው እየጠየቁ ነው።