ዋሽንግተን ዲሲ —
የታይዋንን ነጻ አገርነት የሚደገፉ ሰዎች በእድሜ ልክ ወንጀለኝነት ይመደባሉ ሲሉ በቻይና የታይዋን ጉዳዮች ቢሮ ቃል አቀባይ ዛሬ አርብ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡
ታይዋንን እንደራሷ ግዛት አድርጋ በምትቆጥራት ቻይና እና ራሷን እንደ ነጻ አገር በምትቆጥረው ደሴቲቱ ታይዋን መካከል፣ ያለው ውጥረት እየተባባሰ ከመጣ ወዲህ፣ ቻይና ነጻነትን የሚደግፉ ሰዎችን ለመቅጣት፣ አቋሟን በግልጽ ስታሳውቅ፣ ይህ የመጀመሪያው መሆኑም ተገልጿል፡፡
የቻይናው ጽ/ቤት በስም ጠርቶ ከፈረጃቸው መካከል የታይዋን መሪ ሱ ሴንግ ቻንግ፣ የፓርላማው ቃል አቀባይ ዩ ሲ ኩን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጆሴፍ ዉ ይገኙበታል፡፡
የታይዋይን ነጻ አገርነት በግ ንባር ቀደም ይደግፋሉ የተባሉትን እነዚህ ሰዎች ጨምሮ በጥቁር መዝገብ ውስጥ የተመዘገቡ ሌሎች ሰዎች ከቻይና ካሉ ድርጅቶችም ሆነ ሰዎች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዲኖራቸው የማይደረግ መሆኑም በዘገባው ተመልክቷል፡፡