በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካናዳ የህዋዌን ሥራ አፈጻሚ በመልቀቋ ቻይናም ሁለት ካናዳውያንን ለቀቀች


የቻይናው ኩባንያ ሁዋዌ ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ሜንግ ዋንዙ እንደተለቀቁ ቻይና ሲደርሱ የሚያሳይ ምስል
የቻይናው ዜና አገልግሎት አውጥቷል
የቻይናው ኩባንያ ሁዋዌ ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ሜንግ ዋንዙ እንደተለቀቁ ቻይና ሲደርሱ የሚያሳይ ምስል የቻይናው ዜና አገልግሎት አውጥቷል

ቻይና እና ካናዳ የእገታ ዲፕሎማሲ ወይም ሆስፕቴጅ ዲፕሎማሲ እየተባለ በተጠራውና በየፊናቸው ይዘዋቸው የነበሩ ዜጎቻቸውን በትናንትናው እለት መልቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡

እኤአ በ2018 በዩናይትድ ስቴትስ ጥያቄ ካናዳ የቻይናው ኩባንያ ሁዋዌ ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ሜንግ ዋንዙ በቁጥጥር ሥር ባዋለችበት ሁለተኛው ሳምንት ቻይና ደግሞ ማይክ ስፓቮርና ማይክ ኮቪርግ የተባሉ ሁለት የካናዳ ዜጎችን በቁጥጥር ስር ማዋሏን አስታውቃ ነበር፡፡

ቻይናይቷ ሜንግ በዩናትድ ስቴትስ ተከሰው በካናዳ የተያዙት በሚመሩት ድርጅት ስም ከባንኮች ጋር በተደረገ ግብይት ማጭበርበር ፈጸማዋል በሚል ነው፡፡

ቻይናም በበኩሏ 2ዓመት ከግማሽ ለሚሆን ጊዜ ያሰረቻቸውን የካናዳ ዜጎች የለቀቀች ሲሆን ወደ አገራቸው የተሳፈሩት ሶስቱም ዜጎች በዛሬው እለት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ቻይና የካናዳ ዜጎችን በመልቀቋ የተሰማቸውን ደስታ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር እንደሚጋሩ አስታውቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG