ዋሺንግተን ዲሲ —
በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ውስጥ እጅግ ክፉ ከሚባሉ ነፍሰ-ገዳዮች አንዱ የሆነው ቻርልስ ማንሰን በሰማንያ ሦስት ዓመት ዕድሜው ወኅኒ እንዳለ ዛሬ ሞቷል።
በ1961 ዓ.ም (በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር) በሁለት ሌሊቶች እርሱና ሌሎች ስድስት ግብር አበሮቹ ሎስ አንጀለስ ከተማ ውስጥ በሰባት ሰዎች ላይ ለፈፀሟቸው አሰቃቂ ግድያዎች ላለፉት አርባ አምስት ዓመታት ያህል በእሥር ላይ ቆይተዋል።
ማንሰን የሞተው በተፈጥሮ ምክንያት መሆኑን የካሊፎርኒያ የማረሚያና የማቋቋሚያ መሥሪያ ቤት አስታውቋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ