በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከቻይና ጋር መሻሻልን አሳይቷል


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የንግድ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከቻይና ጋር ጥሩ መሻሻል መከሰቱን ገለፀዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የንግድ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከቻይና ጋር ጥሩ መሻሻል መከሰቱን ገለፀዋል።

ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ማለዳ በትዊተር ባስተላለፉት መልዕክት “ቻይና ከፍርተኛ ብዛት ያላቸው ተጨመሪ የእርሻ ምርቶች ለመግዛት ተስማምታለች። ይህም ገብሬዎቻችን በብዙ ዓመታት ውስጥ ካላገኙዋቸው በጣም ጥሩ ነገሮች አንዲ ነው” ብለዋል።

ዩናይትድ ስቴትስና ቻይና ወደ ውጭ በሚልክዋቸው ሸቀጣሸቀጦች ላይ አዲስ ከባድ ቀረጦች ከመደንገግ ለመቆጠብ መስማማታቸውን የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስትር ስቲቭን ምኑችን አስታውቀዋል። ቤጂንግ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያለውን የንግድ ልውውጥ ማነስን ለማስተካከል ስትል ከበፊቱ የበዛ የአሜሪካ ዕቃዎችን ለመግዛት ባለፈው ቅዳሜ በመስማማትዋ ነው ከፍተኛ ቀረጥ መደንገጉን ያቆሙት።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በትዊተር መልዕክት ያስተላለፉት ታድያ ከሥምምነቱ በኋላ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG