በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና የካናዳ ዜግነት ያላቸው ሰው በቁጥጥር ሥር አውላለች

ቻይና ከሣምንት በፊት አንድ ካናዳዊ የቻይና ቴክኖሎጂ ከፍተኛ አመራር ማሠሯን ተከትሎ ሌላ ሁለተኛ የካናዳ ዜግነት ያላቸው ሰው በቁጥጥር ሥር አውላለች።

ቻይና ከሣምንት በፊት አንድ ካናዳዊ የቻይና ቴክኖሎጂ ከፍተኛ አመራር ማሠሯን ተከትሎ ሌላ ሁለተኛ የካናዳ ዜግነት ያላቸው ሰው በቁጥጥር ሥር አውላለች።

ታሣሪው - የፔከቱ የባህል ልውውጥ ዳይሬክተር ማይክል ስፓቮር መሆናቸውን የካናዳ ባለሥልጣናት አረጋግጠዋል። ቢሯቸው በቻይናና ሰሜን ኮሪያ መካከል የስፖርትና የትምህርት ልውውጦችን የሚያቀነባብር ነው ተብሏል።

ማይክል ስፓቮር የት እንደሆነም ሆነ ለምን እንደታሠሩ የሚገልፅ ሌላ መረጃ የለም። የቀድሞው ካናዳዊ ዲፕሎማት ማይክል ኮቭሪግ ቤጂንግ ውስጥ ተይዘው የታሠሩት፣ የሃገሪቱን ብሄራዊ ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል ድርጊት ፈፅመዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸው ነው ሲሉ፣ የቻይና ባለሥልጣናት ትላንት ተናግረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG