በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና ወደሰሜን ኮሪያ የነዳጅ ዘይት አላኩም ስትል አስተባበለች

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ውሳኔዎችን ተላልፋ ወደሰሜን ኮሪያ ነዳጅ ዘይት ልካለች ብለው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ የወነጀሏት ቻይና “አላደረኩም” ስትል አስተባብላለች፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ውሳኔዎችን ተላልፋ ወደሰሜን ኮሪያ ነዳጅ ዘይት ልካለች ብለው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ የወነጀሏት ቻይና “አላደረኩም” ስትል አስተባብላለች፡፡

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ቃል አቀባይ ሁዋ ቹንዪንግ ዛሬ ቤጂንግ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል

“የፀጥታ ምክር ቤቱን ውሳኔዎች ሙሉ በሙሉ በጥብቅ ሥራ ላይ በማዋል ላይ ነች፡፡ ዓለምቀፍ ግዴታዎቻችንን እያሟላልን ነን” ብለዋል።

ቻይና ማዕቀቦቹን እያስከበርኩ ነኝ ብላ አጥብቃ ብትከራከርም ዩናይትድ ስቴትስ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ግን አሁንም ክፍተቶች አሉ ብለው ይጠራጠራሉ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ትናንት ባወጡት ትዊታቸው ቻይና ወደሰሜን ኮሪያ ነዳጅ እንዲላክ መፍቀዱዋ በጣም አሳዝኖኛል ብለዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG