በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና በዩናይትድ ስቴትስ ዕቃዎች ላይ ቀረጥ የመደንገግ ዕቅድ እንዳላት አስታወቀች


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ቻይና የ50 ቢልዮን ዶላር ቀረጥ በዩናይትድ ስቴትስ ዕቃዎች ላይ የመደንገግ ዕቅድ እንዳላት ዛሬ አስታወቀች። ዩናይትድ ስቴትስ ለደነገገችው ተመሳሳይ ቀረጥ ምላሽ መሆኑ ነው።

ቻይና የ50 ቢልዮን ዶላር ቀረጥ በዩናይትድ ስቴትስ ዕቃዎች ላይ የመደንገግ ዕቅድ እንዳላት ዛሬ አስታወቀች። ዩናይትድ ስቴትስ ለደነገገችው ተመሳሳይ ቀረጥ ምላሽ መሆኑ ነው።

ቻይና የወሰደችው እርምጃ በ106 የአሜሪካ ምርቶች ላይ በ25 ከመቶ ከፍ የሚል ቀረጥ ይደነገጋል። የአይሮፕላን፣ የመኪኖችና የቦለቄ ምርቶችን ያካትታል።

የቻይና የንግድ ሚኒስቴር እርምጃ እንደሚወስድ ያስታወቀው ዩናይትድ ስቴትስ ቀረጥ ከፍ የምተዳርግባቸውን የቻይና እቃዎች ዝርዝር ከጠቀሰች ከ11 ሰዓታት ያነሰ ጊዜ ካለፈ በኋላ ነው። መቼ በተግባር ላይ ይውላል? የሚለው ጥያቄ የሚወሰነው የአሜሪካ ቀረጦች መተግበር ላይ መሆኑን የንግድ ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።

የዩናይትድ ስቴስ ፕሬዚዳንት ትረምፕ በቻይና ምርቶች ላይ የ50 ቢልዮን ዶላር ቀረጥ እንደሚደነገጉ ባለፈው ወር አስታውቀዋል። ትላንት ደግሞ በ1,300 ዕቃዎች ላይ ቀረጥ እንዲጣል የአሜሪካ የንግድ ተወካዮች ሃሳብ አቅርበዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG