በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻድ መራጮች ሁንታውን ይረዳል የተባለውን አዲስ ሕገ መንግሥት ደገፉ


ሴቶች ድምፃቸውን ለመስጠት ወረፋ ይዘው
ሴቶች ድምፃቸውን ለመስጠት ወረፋ ይዘው

ቻዳውያን፣ ተቺዎች የሁንታውን መሪ ማሃማት ኢድሪስ ዴቢን ስልጣን የሚያጠናክር ያሉትን፣ አዲስ ሕገ-መንግስት ደግፈው ድምፅ ሰጥተዋል።

በዚህ በታህሳስ ወር መጀመሪያ ላይ በተካሄደው ህዝበ ውሳኔ፣ 86 በመቶ መራጮች የድጋፍ ድምፅ ሰጥተዋል ሲል ምርጫውን ያካሄደው የመንግሥት ኮሚሽን ትናንት ዕሁድ አስታውቋል። የመራጮች ተሳትፎ 64 ከመቶ እንደሆነም አመልክቷል።

የቻድ ወታደራዊ ባለስልጣናት ህዝበ ውሳኔው “በሚቀጥለው ዓመት ለሚደረገው ምርጫ ወሳኝ እርምጃ ነው” ሲሉ ገልፀውታል። እ.አ.አ በ2021 የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ ከአማፂያን ጋር በተካሄደ ግጭት በጦር ሜዳ ላይ ከተገደሉ በኋላ ስልጣን የያዘው ጦር ሥልጣኑን ወደ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ለማሽጋገር ቃል ገብቶ ነበር።

አዲሱ ሕገ መንግስት ቻድ ነጻ ከወጣችበት ግዜ ጀምራ የምትተዳደርበትን አንድ ማዕከላዊ መንግሥት የሚያፀና ሲሆን፣ አንዳንድ ተቃዋሚዎች ፌዴራላዊ መንግሥት እንዲመሰረት ጥሪ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ተቃዋምሚዎቹ ሁንታው የህዝበ ውሳኔውን ሂደት በበላይነት ተቆጣጥሯል ሲሉም እራሳቸውን ከምርጫው አግልለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG