በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቻድ ወታደራዊ አገዛዝ አብቅቶ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ቃለ-መሃላ ፈፀሙ


የሽግግር ፕሬዚዳንት የሆኑት ጄኔራል ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ
የሽግግር ፕሬዚዳንት የሆኑት ጄኔራል ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ

ቻድ በዚህ ወር መጀመሪያ ባካሄደችው ምርጫ ያሸነፉት ማሃማት ዴቢ ኢትኖ ዛሬ ሐሙስ ቃለ-መሃላ በመፈፀም ከሦስት ዓመት በፊት ስልጣን ከተቆጣጠሩ በኃላ ወደ ዲሞክራሲያዊ አገዛዝ ለመሻገር የተደረገውን አከራካሪ ሂደት አጠናቀዋል።

ዴቢ ኢትኖ ሥልጣኑን የተረከቡት፣ አገሪቱን ለሦስት አስርት ዓመታት ከገዙ በኃላ እ.አ.አ በ2021 ከአማፂያን ጋር ሲዋጉ ከተገደሉት አባታቸው ሲሆን ከሦስት አመታት ወታደራዊ አገዛዝ በኃላ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የቆየው ምርጫ በሚያዚያ 28 ተካሂዷል።

ይህ በእዲህ እንዳለ ተፎካካሪያቸው የነበሩት እና የምርጫውን ውጤት የተቃወሙት ሱክሴ ማስራ ረቡዕ እለተ ከጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣናቸው መልቀቃቸውን ረቡዕ እለት አስታውቀዋል። ማስራ ዴቢ ኢትኖ ስልጣናቸውን ማራዘማቸውን በመቃወም እ.አ.አ በ2022 ከአገር ተሰደ የነበረ ቢሆንም ባለፈው አመት ወደአገራቸው ተመልሰው የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት ተሰጥቷቸው ነበር።

ዴቢ ኢትኖ በመጀመሪያው ፕሬዝዳንታዊ ንግግራቸው፣ መንግስታቸው የቻድን የግብርና ዘርፎች በማሳደግ እና በትምህርት፣ በውሃ አቅርቦት እና በጤና አጠባበቅ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ላይ ትኩረት ያደርጋል ብለዋል። የተለያዩ የምዕራብ አገራት መንግስታትም የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላልፈውላቸዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG