የቻድ ወታደራዊ መንግሥትና አማጽያን ከብሄራዊ እርቁ በፊት የተኩስ አቁም ለማድረግ ተፈራረሙ፡፡
ቻድ ውስጥ በመዋጋት ላይ የሚገኙት የቻድ ወታደራዊ መንግሥትና የተወሰኑት አማያጽን ቡድኖች ነሀሴ 14 2014 ዓ.ም በአገሪቱ መዲና ንጃሜና ላይ ከሚያደርጉት ብሄራዊ እርቅ በፊት ኳታር ላይ ዛሬ የሥምምነት ቃል ተፈራርመዋል፡፡
በስምምነቱ መሰረት መንግስት በአጎራባች አገር በሚገኙ አማጽያን ላይ ወታደራዊም ሆነ የፖሊስ ዘመቻዎችን እንደማያደርግ ቃል መግባቱ ሲገልጽ አማጽያኑም የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸው ተመልክቷል፡፡
ይሁን እንጂ በቻድ የለውጥና የሥምምነት ግንባር እያለ ራሱን የሚጠራው ትልቁ የአማጽያን ቡድን በሥምምነቱ ቃል ባለመስማማቱ በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ላይ በተካሄደው ፊርማ አለመካተቱ ተነገሯል፡፡