በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻድ ሽግግር ወታደራዊ አስተዳደር ከአማጺ ቡድን ጋር እንደማይደራደር አስታወቀ


አዲሱ የቻድ የሽግግር ወታደራዊ አስተዳደር በሰሚኑ የሀገሪቱ ክፍል ከሚንቀሳቀሰው አማጺ ቡድን ጋር እንደማይደራደር አስታወቀ። ይልቁንም አጎራባችዋን ኒጀርን የቡድኑን መሪ ለመያዝ እንድታግዘው ጠይቋል።

የቻድ ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢን ህልፈት ተከትሎ ባለፈው ሳምንት ሥልጣን የያዘው ወታደራዊ ምክር ቤት ቃል አቀባይ አዜም ቢርማንዶዋ በሰጡት ቃል "ከህገ ወጦች ጋር ሽምግልና የምንገባበትም የምደራደርበትም ወቅት አይደለም፤ ጦርነት ላይ ነን" ብለዋል።

"አማጺ ናቸው። በቦምብ የምንደበደባቸውም በዚያ ምክንያት ነው። ጦርነት ላይ ነን አለቀ ይኸው ነው" ብለዋል ቃል አቀባዪ።

ለበርካታ ዓመታት ሥልጣን ላይ የቆዩት የቻድ ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢ የጦር ሰራዊቱ ባስታወቀው መሰረት ባለፈው ሳምንት ህይወታቸው ያለፈው በብዙ መቶዎች የተቆጠሩ አማጺያን በተገደሉበት ውጊያ ግንባር ላይ ተመትተው በደረሰባቸው ጉዳት ምክንያት ነው።

መቀመጫውን ሊቢያ አድርጎ የሚነቀሳቀሰው በአህጽሮት “ፋክት” ተብሎ የሚጠራው አማጺ ቡድን መሪ ማሃማት ማሃዲ አሊ አምልጦ ኒጀር መግባቱን የሚናገረው የቻድ ወታደራዊ መንግሥት አድኖ ለመያዝ የኒጀርን ርዳታ ጠይቁዋል።

XS
SM
MD
LG