በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቻድ ምርጫ ተሸናፊው እጩ የምርጫው ውጤት እንዲሰረዝ ጠየቁ


ፋይል፦ ሰዎች ድምፃቸውን ለመስጠት እየተጠባበቁ በኒጃሜና፣ ቻድ እአአ ታኅሣስ 17/2023
ፋይል፦ ሰዎች ድምፃቸውን ለመስጠት እየተጠባበቁ በኒጃሜና፣ ቻድ እአአ ታኅሣስ 17/2023

በቻድ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ሁለተኛ ደረጃን ያገኙት ሰክሰስ ማስራ፣ የሕገ መንግስት ም/ቤቱ የምርጫውን ውጤት እንዲሰርዝ መጠየቃቸውን ትላንት እሁድ አስታውቀዋል።

ማስራ ጥያቄያቸውን ያስገቡት በደርዘን የሚቆጠሩ የፓርቲያቸው የማሕበረሰብ አንቂዎች በተጭበረበረ ሰነድ የምርጫ ቆጠራ ሥራ ውስጥ ገብተዋል በሚል በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ተከትሎ ነው።

ማስራ ካስገቡት ጥያቄ ጋራ፣ የምርጫ ኮሮጅዎች ሲታጨቁ፣ ዛቻዎች፣ ስርቆቶች እንዲሁም ወታደሮች የምርጫ ኮሮጆችን “ሌላ ቦታ ይቆጠራሉ” በሚል ይዘው ሲሄዱ የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን ማያያዛቸውን አስታውቀዋል።

የሁንታው መሪ ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ በ61.03 በመቶ ማሸነፋቸውንና ማስራ ደግሞ 18.53 በመቶ ማግኘታቸውን የሃገሪቱ የምርቻ ማለሥልጣናት ባለፈው ሐሙስ አስታውቀዋል። ማስራ ግን ቀድመው አሸናፊነታቸውን አውጀው የዴቢ ቡድን ምርጫውን ሊያጭበረብር እንደሚሞክር አስታውቀው ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG