በቻድ የሽግግር ፕሬዝደንት የሆኑት ጀኔራል ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ በሥልታናቸው ለመቀጠል ሙከራ ላይ ናቸው በሚል የተበሳጩ ወጣቶች የምርጫ ዘመቻ ፖስተሮቻቸውን ከየመንገዱ ቀደው ሲጥሉ ተስተውለዋል።
የቀድሞው ተቃዋሚ እና የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰክሰስ ማስራን ጨምሮ በመጪው ሰኞ ለምርጫ የሚቀርቡት የዴቢ ተቀናቃኞች በመቶዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው እንደተያዙ አስታውቀዋል።
የቻድ መዲናን ኢንጀሜናን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች የዴቢ የምርጫ ፖስተሮችን ተቃዋሚ ሰልፈኞች በማውረድ ላይ ናቸው።
በተለያዩ ማኅበራዊ መድረኮች በተሰራጩ ምስሎች፣ በቻድ ለውጥ እንዲደረኛ “የዴቢ ሥርወ መንግስት” ብለው የገለጹት አገዛዝ እንዲያከትም ሲቪሎች ጠይቀዋል።
ጀኔራል ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ ከሶስት ዓመታት በፊት ወደ ሥልጣን የመጡት ሃገሪቱን ለ30 ዓመታት የገዙት አባታቸው ኢድሪስ ዴቢ በአማጺያን መገደላቸውን ተከትሎ ነው።
ጀኔራል ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ፣ የምርጫ ዘመቻቸው እንቅፋት እንደገጠመው፣ የዘመቻ ሠራተኞቻቸው ጥቃት እየተፈጸመባቸው እንዲሁም ፖስተሮቻቸው እየተወገዱ እንደሆነ በዚህ ሳምንት በቴሌቪዥን ቀርበው አስታውቀዋል።
መድረክ / ፎረም