በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻድ ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢ መሞታቸው ተገለጸ


የቻድ ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢ
የቻድ ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢ

ፕሬዚዳንቱ ትናንት ሰኞ ወደ ዋና ከተማዋ ወደ ኢንጃሜና እየገፉ ናቸው ከተባሉት አማጽያን ጋር የሚዋጉትን ወታደሮች ወደውጊያው ግንባር ተጉዘው በመጎብኘት ላይ እንዳሉ መገደላቸውን ነው የቻድ የጦር ሠራዊት ቃል አቀባይ ያስታወቀው።

የስድሳ ስምንት ዓመቱ ዴቢ በቅርቡ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለስድስተኛ የሥልጣን ዘመን መመረጣቸው ይታወሳል። የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት ሪፖርቱን የሚያረጋግጥ መግለጫ እስካሁን አላወጣም።

ኢድሪስ ዴቢ እአአ በ1990 በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን ከያዙ ጀምረው ለሠላሳ ዓመታት ሥልጣን ላይ ቆይተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት በተካሂደው ምርጫ ሰባ ዘጠኝ ከመቶውን ድምፅ አግኝተው ለስድስተኛውን የሥልጣን ዘመን መመረጣቸውን ነው ይፋዊ የምርጫው ውጤቶች ያሳዩት።

XS
SM
MD
LG