በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእሁዱ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ምርጫ ከወዲሁ አስግቷል


በሁከት የታመሱ ተፈናቃይ ስደተኞች የማዕካለዊ አፍሪካ ሪፐብሊክንና የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን በሚያዋስነው ድንበር አቅራቢያ
በሁከት የታመሱ ተፈናቃይ ስደተኞች የማዕካለዊ አፍሪካ ሪፐብሊክንና የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን በሚያዋስነው ድንበር አቅራቢያ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰአብዊ መብት ቢሮ፣ በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በመጭው እሁድ በድጋሚ ከሚካሄደው የህግ አውጭዎች ምርጫ ጋር ተያይዞ ፣ ያገረሸው አመጽ ያሳሰበው መሆኑን አስታውቋል፡፡

ባለፈው ታህሳስ በመካከለኛው የአፍሪካ ሪፐብሊክ የተካሄደው የምክር ቤት አባላት ምርጫ ከፍተኛ መጭበርበር፣ የሰብአዊ መብት ጥሰትና አመጽ የበዛበት በመሆኑ በዚህኛውም ምርጫ ተመሳሳይ ነገር ይፈጸማል የሚለው ስጋት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለሥልጣናትን አሳስቧል፡፡

ከጥቅምት እስከ ህዳር ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ የድርጅቱ ሰብአዊ መብት ቢሮ 185 የሚሆኑ የሰብ አዊ መብት ጥሰቶችን መዝግቧል፡፡ የሰአብዊ መብት ቢሮው ቃለ አቀባይ ራቪን ሻማዳሳኒ ከነዚህ ጥሰቶች ውስጥ አብዛኛውን ኃላፊነት የሚወስዱት ታጣቂዎቹ አማጽያን ናቸው ይላሉ፡፡

"ሰላማዊ ዜጎችን ገድለዋል አፍነዋል፡፡ ህዝቡን ለማስፈራራት ዝምብለው ይተኩሳሉ፡፡ የተባበሩት መንግሥታ ድርጅት ሰላም አስከባሪዎችን በማጥቃት ባለፈው ታህሳስና ጥር ወር ላይ ሰባት ሰዎችን ገድለዋል፡፡ የምርጫ ጣቢያዎችን ያወድማሉ፣ የምርጫ ቁሳቁሶችን ከጥቅም ውጭ ያደርጓቸዋል፡፡ የመንግሥት ወኪሎችና ደጋፊዎቻቸው ሰላማዊ ዜጎችን ይገድላሉ አካላዊ ስቃይ ያደርሳሉ ያገኙትን ሁሉ ደስ እንዳላቸው ከየመንገዱ እየያዙ ያስራሉ፡፡"

ቃል አቀባይዋ የመንግሥት የጸጥታ ኃሎች የሰአብአዊ መብት ድርጅት ንብረቶችን ሳይቀር እንደሚዘርፉም አስታውቀዋል፡፡ ባለፈው ታህሳስ የተፈጸመውን አመጽና ሁከት ተከትሎ መንግሥት የሰዐት እላፊ ገደብ የጣለ ሲሆን ፣ ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም አውጥቷል፡፡

ቃለ አቀባይዋ እርምጃዎቹ በአገሪቱ አለመረጋጋትን የፈጠሩ ሲሆን የሰአብዊ መብት ቀውሶችንም ማባባሳቸውን ተናግረዋል፡፡ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ እኤአ 2013 ላይ አመጸኞቹ ፕሬዚዳንት ፍራንሷ ቦአዚዝን ከሥልጣን ሲያነሱ ከተፈጠረው ሁኔታ የባሰ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡ ስለዚህ መንግሥት በሰብአዊ መብት ጥሰትና የምርጫ ሂደቱን የሚያውኩ ተጠያቂዎችን በሙሉ በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲያቀርብ ጠይቀዋል፡፡

የእሁዱ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ምርጫ ከወዲሁ አስግቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:25 0:00


በዓለም ዙሪያ በበርካታ የተለያዩ አካባቢዎች እንደምታዩት አለመከሰስና ተጠያቂ አለመሆን ሌሎችን ሊያበረታታና ተጨማሪ ጥሰቶችን ሊያጠናክር ይችላል፡፡ ስለዚህ መንግሥት እንደዚህ ያሉ ዓይነት ጥሰቶችን እንደማይታገስና እንዲህ ያሉ ሰዎች ተጠያቂ መሆናቸው በማሳየት ግልጽ መልእክት ማስተላለፍ አለበት፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ባለሥልጣናት የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክን ጸጥታና የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቁ ኃላፊነት የመንግሥት ጸጥታ ሠራተኞች ኃላፊነት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ታጣቂ በሆኑ ወገኖች ሁሉ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ላይ በቂ ምርመራ ተደርጎባቸው ተጠያቂዎች ለፍርድ መቅረብ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

(የቪኦኤ ዘጋቢ ሊዛ ሽላይን ከጄኔቭ ከላከችው ዘገባ የተወሰደ፡፡)

XS
SM
MD
LG