በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ወንዶች የእግር ኳስ ግጥሚያ - በአሥመራ


አሥመራ
አሥመራ

የኢትዮጵያ ከ15 ዓመት በታች ወንዶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ኤርትራ በምታስተናግደው የምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማኅበራት ካውንስል - ሴካፋ ሻምፕዮና ላይ ለመሳተፍ ነገ ወደ አሥመራ እንደሚሄድ ታውቋል።

አሥመራ ላይ በሚካሄደው በታሪክ የመጀመሪያ በሆነው የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ወንዶች የእግር ኳስ ግጥሚያ መክፈቻ ላይ አስተናጋጇ ኤርትራ ከቡሩንዲ ጋር እንደሚጫወቱ መርኃግብሩ ያሳያል።

በሁለት ምድቦች ተከፍሎ በሚካሄደው ውድድር የኢትዮጵያ ከ15 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በምድብ ሁለት ከዩጋንዳ፣ ከታንዛንያ፣ ከደቡብ ሱዳን እና ከርዋንዳ ጋር የተደለደለ ሲሆን የኢትዮዽያ ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታውን የሚያደርገው ከነገ በስተያ ቅዳሜ ከዩጋንዳ ጋር እንደሚሆን ታውቋል።

የፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ዳይሬክተር መኮንን ኩሩ እንዳሉት የኢትዮዽያ ከ15 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ወደ አስመራ መጓዙ የሁለቱን ሀገሮች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንደሚያጠናክር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር መኮንን ብሩ ፌዴሬሽኑ ስለሻምፒዮናው ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ መናገራቸውን ሪፖርተራችን ግርማቸው ከበደ ከአዲስ አበባ ዘግቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኤርትራ ዝግጅቷን ማጠናቀቋንና የሴካፋ ከፍተኛ ባለሥልጣናትም አሥመራ ላይ መግለጫ መስጠታቸውን የአሥመራው ሪፖርተራችን ብርሃነ በርኸ አመልክቷል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ወንዶች የእግር ኳስ ግጥሚያ - በአሥመራ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:00 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG