በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መምፕስ


በመላዋ ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኙ ፍልሰተኞች ተይዘው በሚቆዩባቸው ማዕከሎች ውስጥ በእንግሊዝኛ ስሙ “መምፕስ” በሚባል ቫይረስ ወደዘጠኝ መቶ የሚሆኑ ሰዎች መታመማቸው ተረጋገጠ።

መንጋጋ ቆልፍ፣ ትኩሳት፣ የዕጢ ማበጥ፣ ራስ ምታት እና ሲከፋም መስማት የሚከለክል እና ለማጅራት ገትር ተላላፊ በሽታ የሚጋልጥ ነው ።

በአስራ ዘጠኝ የዩናይትድ ስቴትስ ክፍለ ግዛቶች ባሉ ሃምሳ ሰባት የእስር ማዕከሉች የተዛመተው ቫይረሱ ስምንት መቶ ዘጠና ስምንት ሰዎች መታመማቸውን የበሽታዎች ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል ሲስታውቅ፣ ሰላሳ ሶስት የማዕከኦቹ ሰራተኞችም ታመዋል።

ይህ ቫይረስ መከላከያ ክትባቶች ስለሚሰጡ ዩናይትድ ስቴትስ ወስጥ እምብዛም እንደማይከስተ ሲገልፅ፣ ይሁን እንጂ ሰዎች ለተራዘመ ጊዜ ተፋፍገው በሚኖሩበት ሁኔታ የመዛመት ዕድል ያገኛል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG