በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲስ ኮሮናቫይረስ ተጋላጮች 93 ከመቶው በዴልታው ዝርያ የተያዙ ናቸው - ሲዲሲ


ሲዲሲ
ሲዲሲ

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከጠቅላላው አዲስ የኮሮናቫይረስ ተጋላጮች ውስጥ ዘጠና ሶስት ከመቶው በዴልታው ዝርያ የተያዙ ናቸው ተባለ።

የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል ሲዲሲ ያለፈውን ሳምንት የወረርሺኙን ይዞታ አስመልክቶ ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው በፈረንጆች ሃምሌ ወር የመጨረሻዎቹ ሁለት ሳምንታት ለቫይረሱ ከተጋለጡት ሰዎች ውስጥ ዘጠና ከመቶ የሚበልጡትን የያዛቸው ዴልታ የተባለው የቫይረሱ ዝሪያ እና ሌሎቹም አስጊ ናቸው የተባሉ የዴልታው ተቀጥላ ዝርያዎች ናቸው።

በተጨማሪም ባለፈው ሳምንት በየቀኑ ለቫይረሱ የተጋለጡ ሆነው የተገኙት ሰዎች ቁጥር ከስድሳ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ በላይ መሆኑን የገለጸው ሲዲሲ በቀደመው ሳምንት አርባ ሺህ ስድስት መቶ ከነበረው የዕለታዊ ተያዥች ቁጥር ከስድሳ አራት ከመቶ በላይ የሚበልጥ መሆኑን ጠቁሟል።

ይህ ያሁኑ አሃዝ ወረርሺኙ እጅግ ተስፋፍቶ ከነበረበት እና በየቀኑ ሦስት መቶ ሺህ አዲስ ተያዦች ይመዘገቡ ከነበረበት ወቅት ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ቢሆንም ባለፈው ግንቦት ወር በቀን ወደስምንት ሺህ ወርዶ ከነበረው ጋር ሲነጻጸር ግን ቁጥሩ በእጅጉ እያሻቀበ መሆኑ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG