በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሦስተኛውን የፋይዘርን ማጠናከሪያ ክትባት ሲዲሲ ፈቀደ


የፋይዘርን ክትባት
የፋይዘርን ክትባት

የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል /ሲዲሲ/ የመጀመሪያ የኮቪድ ክትባታቸውን ከስድስት ወር በፊት ወስደው ያጠናቀቁ የተወሰኑ ሰዎች የፋይዘርን ማጠናከሪያ ክትባት መወጋት እንዲችሉ ፈቃድ ሰጥቷል።

የአውሮፓ ህብረት የመድሃኒት ቁጥጥር ቢሮ በበኩሉ ከአስራ ስድስት ዓመት በላይ ለሆኑ ሦስተኛ የፋይዘር ክትባት መከተብን አስመልክቶ በሚቀጥለው ጥቅምት መጀመሪያ ውሳኔ ላይ እንደርሳለን ሲል አስታውቋል።

የአፍሪካ መሪዎች በበኩላቸው የክትባቱ ድልድል የተዛበ መሆኑን በመግለጽ ቅሬታቸውን ማሰማታቸውን ቀጥለዋል።

ትናንት የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፖሳ ለጠቅላላ ጉባኤው ካሉበት በቪዲዮ ባሰሙት ንግግር ሰማኒያ ሁለት ከመቶው የዓለም የክትባት አቅርቦት በባለጸጎቹ ሃገሮች እጅ መሆኑ እና ለባለዝቅተኛ ገቢ ሃገሮች የደረሰው አንድ ከመቶ ብቻ መሆኑ በሰብዓዊ ፍጡራን ላይ መፍረድ ነው ሲሉ ተችተዋል።

የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋም ክትባቱን ለራስ ብቻ ሰብስቦ ማከማቸት ሁሉም ከቫይረሱ ካልተጠበቀ ብቻውን ሊጠበቅ የሚችል የለም ከሚለው መርህ ጋር የሚጋጭ አድራጎት ነው ሲሉ ለጠቅላላ ጉባኤው ባሰሙት ንግግር አሳስበዋል።

XS
SM
MD
LG