በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መጪዉ ብሔራዊ የኢትዮጵያ ምርጫና የመገናኛ ብዙኃን ሚና


ነጻና ሚዛናዊ ምርጫ ለማካሄድ የሁሉንም ተወዳዳሪዎች ፕሮግራም ለሕዝብ የሚያደርስ በነጻነት የሚዘግብ መገናኛ ብዙኃን ወሳኝነት የዲሞክራሲ ባሕልና መሠረትም ነው።

በርካታ ጋዜጠኞች እስር ላይ በሚገኙባትና ያንኑ ያህል ቁጥራቸው የበዛ አገር ጥለው በተሰደዱባት ኢትዮጵያ በነጻነት መዘገብ የሚችሉ ጋዜጠኞች መኖር እያነጋገረ ነው።

ለጋዜጠኞች መብት ከቆሙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አንዱ Freedom House በቅርቡ ስለ አገሮች የነጻ ፕሬስ ይዞታ ባወጣው ዓመታዊ ሪፓርቱ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ቀጥሎ ጋዜጠኞች የታሰሩባት አገር መሆንዋን ዘግቧል። በጸረ ሽብር ሕጉና በወንጀለኛ መቅጫ የተከሰሱ ቢያንስ አስራ ሰባት ጋዜጠኞች በእስራ ላይ እንደሚገኙ ሌሎች በርካቶች እንደተሰደዱ በሪፖርቱ ዘርዝሯል።

የኢትዮጵያ መንግስት ባለ ስልጣናት በተደጋጋሚ “ጋዜጠኛ ሰለሆነ የሚታሰር ማንም የለም። በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ ብቻ ናቸው የታሰሩት፤” ይላሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰለመጪዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ለመዘገብ የሚያስችል ነጻ የመገናኛ ብዙኃን ሕዋ አለ? ከአድማጮች ለቀረቡ ጥያቄዎች የሰጡትን መልስ ጨምሮ በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር የሚገኙ ጋዜጠኞች ተጋብዘው ይወያያሉ።

ውይይቱን ከዚህ ያድምጡ፤
please wait

No media source currently available

0:00 0:28:48 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG