በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አቡነ ፍራንሲስ በቀሳውስት የሚፈፀምን ወሲባዊ ጥቃት አወገዙ

ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በቀሳውስቷ በልጆች ላይ የሚፈፀም ወሲባዊ ጥቃት የመከላከል እንዲህ ያለው አድራጎት ተፈፅሞ ቢገኝ እንኳን እንዳትሸፋፈን የማድረግ ባህል ለማረጋገጥ አስፈላጊው ጥረት ሁሉ መደረግ እንዳለበት ዛሬ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ብፅዕ አቡነ ፍራንሲስ አሳሰቡ።

ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በቀሳውስቷ በልጆች ላይ የሚፈፀም ወሲባዊ ጥቃት የመከላከል እንዲህ ያለው አድራጎት ተፈፅሞ ቢገኝ እንኳን እንዳትሸፋፈን የማድረግ ባህል ለማረጋገጥ አስፈላጊው ጥረት ሁሉ መደረግ እንዳለበት ዛሬ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ብፅዕ አቡነ ፍራንሲስ አሳሰቡ።

ብፁዕነታቸው ይህን ማሳሰቢያ የሰጡት በቅርብ ጊዜ ይፋ እየተደረገ ያለውን በቀሳውስት የተፈፀሙ ድርጊቶች በተመለከተ ለዓለም ካቶሊክ ዕምነት ተከታዮች በፃፉት ደብዳቤ ነው።

ባለፈው ሳምንት አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ የክስ ሰሚ ሕዝባዊ ሸንጎ ይፋ ባደረገው ሪፖርት በሥድስት የፔንሲልቬንያ ክፍለ ሃገር ሃገረ ስብከት ባለፉት ሰባ ዓመታት ውስጥ ከሦስት መቶ በላይ ቀሳውስት ከአንድ ሺህ በሚበልጡ ልጆች ላይ ወሲባዊ ጥቃት አድርሰዋል ብሏል።

አቡነ ፍራንሲስ በደብዳቤቸው ምንም እንኳን እነዚህ አብዛኞቹ ቀድሞ የተፈፀሙ ናቸው ሊባል ቢችልም በብዙዎቹ ሰለባዎች ላይ ያሳደሩትን ጉዳት በየገዜው እየተረዳነው ነው ብለዋል።

ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አሉ ብፁዕነታቸው ወዲያው ዕርምጃ አለመሰዷን በሃፍረት እና በፀፀት ታምናለች። አጥቂዎቹ በብዙ ሰዎች ላይ ያደረሱትን ጉዳትም ትረዳለች።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG