ዋሺንግተን ዲሲ —
የስፔን መንግሥት ካታሎኒያን ራስ ገዝ አስተዳደርዋን የሚገፍፍ ዕቅድ ማውጣቱን ዛሬ ይፋ አድርጓል።
ይህ የሆነው የግዛቲቱ መሪ የነፃነት ውሳኔ ሕዝቡን ዕቅድ እገፋበታለሁ ብለው ማስታወቃቸውን ተከትሎ ነው።
የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያኖ ራጆይ ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ የሕገ መንግሥቱን አንቀፅ 155 ለማንቀሳቀስ ልዩ የካቢኔ ስብሰባ ለማካሄድ አቅደናል ብሉዋል።
አንቀፁ ማዕከላዊው መንግሥት ግዛቲቱን ሁሉንም ወይም ከፊል ራስ ገዝ አስተዳደርዋን እንዲሰርዝ ሥልጣን ይሰጣል።
ቀደም ሲል የካታሎኒያ መሪ ካርልስ ፒዪጅሞንት በሰጡት መግለጫ የስፔን መንግሥት ድርድር ለማካሄድ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ ራስ ገዝ ሥልጣናችንን ለመግፈፍ ከተንቀሳቀሰ የግዛቲቱ ፓርላማ የመገንጠል ውሳኔ ህዝቡን ያስፈፅማል ሲሉ አስታውቀዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ