በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የካታሎኒያ መገንጠል መሪ ስፔይን ገብተው ወጡ


የካታሎኒያ ተገንጣይ መሪ ካርሌስ ፑችዴሞን
የካታሎኒያ ተገንጣይ መሪ ካርሌስ ፑችዴሞን

የካታሎኒያ ተገንጣይ መሪ ካርሌስ ፑችዴሞን በባርሴሎና በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ከታዩ በኋላ ስፔይንን ለቀው ወደ ቤልጂየም ሄዱ።

የፓርቲያቸው ዋና ጸሀፊ ዛሬ ዓርብ በሰጡት መግለጫ ፑችዴሞን ስፔይን ውስጥ እንዲያዙ የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸዋል ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ፑችደሞን ከሀገር በመሸሽ ራሳቸውን በግዞት በሚያኖሩባት ዋተርሉ ቤልጂየም ስለመድረሳቸው እንደማያውቁ ዋና ጸሀፊው ጆርዲ ቱሩል ተናግረዋል፡፡

እኤአ ካታሎኒያን ከስፔይን ለመገንጠል ያደረጉት ሙከራ ከከሸፈ ጀምሮ የካታሎኒያን የነጻነት ጥያቄ ትግል የሚመሩት ፑችደሞን ላለፉት ሰባት ዓመታት መኖሪያቸውን ዋተርሉ አድርገዋል፡፡

እኤአ 2017 ውድቅ ከተደረገው የነጻነት ህዝበ ውሳኔ ጋር በተገናኘ የስፔይን ፍርድ ቤቶች ህገ ወጥ በሆነ መንገድ እንዲወስኑ ተፈጽሟል ከተባለው ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ፑችደሞን ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

ውሳኔውን ህጋዊ ነበር ያሉት ፑይጅዴሞን ግን ክሱ መሰረተ ቢስ ነው ብለዋል።

ቱሩል “ፑችደሞን ወደ ስፔይን የመጡት ስፔይን ውስጥ በቁጥጥር ስር ለመዋል ሳይሆን የፖለቲካ መብታቸውን ለመጠቀም ነበር” ብለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG