ዋሺንግተን ዲሲ —
የካታላን ክልል ፕሬዚዳንት ካርለስ ፒዩጅሞንት የምክር ቤት አባላት የካታሎኒይ የራስ አስተዳደር ቦታን ለመቀልበስ በሰነዘሩት ዛቻ የሚገፉ ከሆነ የስፔን መንግሥት የካታሎኒያ ክልል ለነፃነት ከሚያካሄደው ዘመቻ ጋር የተያያዘውን የፖለቲካ ቀውስ ያባብሳል ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ለሕግ መወሰኛው ምክር ቤት በላኩት ደብዳቤ የታቀደው ከምክንያታዊነት የዘለለ እርምጃ ቢወሰድ በካታሎኒያ ህዝብ ላይ “ቀጥተኛ አንደምታ ይኖረዋል” ብለዋል።
መንግሥት ከባድ ሁኔታ ላለው መፍትሄ ለማግኘት ሲል የካታሎኒያን የውስጥ አስተዳደር መብትን ቢቀለብስ የባሰ ሁኔታ ይፈጠራል ሲሉ ፕሬዚዳንቱ አስጠንቅቀዋል።
የስፔን የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ነገ አርብ በሚያካሄደው ስብሰባ በካታሎኒያ ቀጥተኛ አገዛዝን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ