በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፊደል ካስትሮ ኅልፈት


የቀድሞው የኩባ ፕሬዚዳንት ፊደል ካስትሮ ሩዝ በዘጠና ዓመት ዕድሜአቸው አርፈዋል፡፡

የአሁኑ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት የሆኑት ታናሽ ወንድማቸው ራውል ካስትሮ ናቸው ትናንት ማታ በብሄራዊው ቴሌቪዥን ቀርበው ዜና እረፍታቸውን ይፋ ያደረጉት፡፡

የፊደል ካስትሮ አስከሬን ዛሬ እንደሚቀጠልና ለመጭዎቹም ዘጠና ቀናት ብሄራዊ ኀዘን መታወጁን ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል፡፡

ፊደል ካስትሮ
ፊደል ካስትሮ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለኩባ ሕዝብ የኀዘን መልዕክት አስተላልፈው “የካስትሮን የግል ማንነት ታሪክ ወደፊት ይናገራል” ብለዋል፡፡

ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ካስትሮን “አምባገነን” ብለዋቸዋል፡፡

የቀድሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣን የነበሩት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ስለፊደል ካስትሮ የሚያስታውሱትን ለቪኦኤ አጫውተዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የፊደል ካስትሮ ኅልፈት
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:54 0:00

XS
SM
MD
LG